የቤተሰብ አገልገሎት ዘርፍ

family images1

ወደ ቤተሰብ አገልግሎት ዘርፍ እንኳን ደህና መጡ!

‹…የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።› ኢያሱ 24፤15

ጤናማ ቤተሰብ በእግዚአብሔር ተመስረቶ የክርስቶስን ፍቅር የሚግለፀ እና ከእርሱ ጋር የመኖርን አስፈላጊነትን የሚያንፀባርቅ ተቌዋም ነው። ቤተሰበ የክርስቶስ ፍቅርን የምንማርበት፣ ባል ወይም ሚስት መሆን ምን ማለት እንደሆነ፣  የጠበቀና ዘላቂነት ያለው ግንኙነት ከለሎች ጋር እንዲት እንደምንመሰርት፣ በተገቢው መልኩ ስሚቶቻችንን መግልጽ ፣ በአካል በስነ ልቦና እና በእውቅት ላይ የተነሱ ግጭቶችን ጤናማ በሆነ መልኩ እንዲት እንደምንፈታ፣ በሕይወት የሚገጥሙ ችግሮችን መጋፈጥና ማሸነፍ፣ እራስን በመልካም ስነምግባር ማነጽ፣ እርስ በእርስ መፋቀርና መቀባበል የምንማርበት ማዕከል ነው።

አገልግሎታችን የክርስቶስን ወንግልን በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ በመታገዝ ክርስቲያናዊ የሆነ በፍቅር የተመሰረተ ቤተሰብን መገንባት ነው­።

አገልግሎታችን የሚያካትታቸው

  • ክርስቲያናዊ ቤተሰብ ምን ማለት ነው
  • በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ ደቀ መዝሙርነትን ማጠናከር
  • የክርስቲያን ቤተሰብ ሚና በግልና በማህበር ውስጥ
  • ትዳራቸው አደጋ ላጋጠማው እና ፍችን አማራጭ አድርገው ለሚውስዱ ባለ ትዳሮች የምክር አገልግሎት መስጠት
Advertentie