የስደተኞች አገልገሎት ዘርፍ

refeugee images

ወደ ስደተኞች አገልግሎት ዘርፍ እንኳን ደህና መጡ!

“ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።”  (ማቲ 25፤35-36)

ስደተኛነት በበዛበት በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያን ከምድራቸው ማለትም በአገሮች መካከል በሚነሳ ግጭት፤ በዘር ማጥፋት፤ በሃይማኖት እና በፖለቲካ ምክንያት በሚደረግ ጭፍጨፋ እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ወደ ነዘርላንድ የገቡ ስደተኞችን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ በመድረስ የወንጌል ባላደራነታችንን እንወጣለን። አገልግሎታችን ለስደተኞች  የክርስቶስን ወንጌልን በፍቅር ማድረስ ነው።

ቤተክርስቲያን ስደተኞችን የምትንከባከበት ምክንያቶች፤-

ዘፍ 1፤26-28 ‘የእግዚአብሔር ባህሪ ተካፋነታችንን ለማሳየት’’፥ ዘፍ 12:10; 26:1; 41:57; 42:6; 43:1-7 የቀደሙት መንፈሳዊ አባቶቻችን ስደተኞች ስለነበሩ’፥ ዘዳ 10፤18-19 ’ እግዚአብሔር ለስደተኞች ስለሚፈርድ’ ሮሚ 12፤13፥ ዕብ 13፤2፥ 1ኛ ጲጥ4፤9፥ ሉቃ 14፤18-19 ‘እንግዶችን ተቀባይ መሆን ስለሚገባ

ስደተኞችን የምንረዳባቸው መንገዶች

 • በሃይል ስለተሰደዱ ሁሉ በፀሎት ማገዝ
 • የሃገሩ ሰው ስደተኞችን የሚወድ ልብ እንዲኖረው መፀለይ
 • ስደተኞች የሚፈልጉትን እርዳታዎች ማግኘት የሚችሉበትን መንገዶች ማሳየት
 • በገቡበት አዲስ ሃገር የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች እንዴት እንደሚወጡት ማሳየት

ከሌሎች ቤተክርስቲያናት፣ የስደተኛ መርጃ ድርጅቶች እና በጎ አድራጊ ግለሰቦች ጋር በመተባበር አዲስ ለሚመጡ ስደተኞች መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ማገዝ፤ ለምሳሌ-

 • ምግብ እና ለወቅቱ የአየር ጠባይ የሚስማማ ልብስና ጫማ መስጠት፣
 • ትራንስፖርት ማቅረብ
 • ከተለዩዋቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ መርዳት
 • ባቅራቢያቸው የሚገኝ ቤተክርስቲያን በመፈለግ ማገናኘትና
 • በቌንቌቸው የተፃፈ መፀሐፍ ቅዱስ መስጠት
 • ያሉበትን አገር ቌንቌና ባህል እንዲያውቁ መርዳት
 • ለልጆቻቸው የትምህርት አሰጣጥ ዘዲውን ማስተዋዋቅና የቤት ስራ መርዳት
Advertentie