እርስዎም ተጋብዘዋል!

እንኳን በሰላም ወደኔዘርላንድ መጡ!!

በቅርቡ በእንግድነት ወደ ኔዘርላንድ መምጣትዎትንና በፍሪስላንድ ወይም በክሮኒንገን ክልል ዙሪያ ነዋሪ መሆንዎትን ተረድተናል ለእርሰዎና ለቤተሰብዎም የፍሪስላንድ ወይም የክሮኒንገን ማህበረሰብ መልካም አቀባበል እንዳደረጉላችሁና የተመቸ የማረፊያ ስፈራ እንዳገኛችሁም ተስፋ እናደርጋለን፡፡
እንደሚታወቀው የለመዱትን ስፈራ ለቆ ወደሌላ ስፈራ ለውጥ ሲደረግ ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች እንደሚገጥሙ ይታመናል አዲስ ባህል፣ ቋንቋ፣ አመጋገብ፣ የተለየ የአየር ጸባይ፣ የተለየ የትምህርት ስርዓት፣ የስራ ዕጥረት፣ የቤተሰብ ናፍቆት፣ ከነዋሪው ማህበረሰብ ጋር በቀላሉ ለመቀላቀል አስቸጋሪነቱን እንረዳለን ፡፡
ሁሉን ነገር በዚህች እጭር መልዕክት መናገር ባይቻልም አንድ ነገር ግን እንገነዘባለን እርስዎና ቤተሰብዎ ያለፉባቸው አሁንም እያለፉባችው ያሏቸው መንገዶች እግዚያብሄር በመልካም እንደሚለውጣቸው፣ እርስዎንም ወደዚህ ስፍራ ሲያመጣዎ እንዳልተሳሳተና አላማ እንዳለው የእግዚያብሄር ቃል ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28 ላይ “ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።” በማለት ያረጋግጣል።
በፍሪስላንድ እና በክሮኒንገን ዙሪያ የምንኖር ወንድሞችና እህቶችም በትንቢተ ኢሳይያስ 55:6 ላይ እንደተጻፈው “ እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት ” እንደሚል ከተለያየ ስፈራ ከክፉ ሃሳብና እቅድ አስመልጦ ከሞትም አትርፎ በዚህ ስፈራ ያስቀመጠን ወገኖች የእግዚአብሄርን ውላታ በማስታወስ ልናመልከው ልናገለግለውና ልንገዛለትና እንደፈቃዱም ልንኖር ህብረት አድርገናል።
ስለሆነም ርኆቦት ወንጌላዊት ቤተክርስትያን እንኩዋን እግዚያብሄር በሰላም ወደዚህ ስፈራ አመጣችሁ እያለች በዚህ በፍሪስላንድ እና በክሮኒንገን ክልል በሚቆዩባቸው ግዚያቶች ውስጥ ከቤተክርስትያን ጋር ከዚህ በታች በተግለጹት የቤተክርስትያን ፕሮግራሞች ላይ በመገኘት ከእኛ ጋር ህብረት እንዲያደርጉ እየጋበዝንዎት እርስዎ በፈቀዱትና ቤተክርስትያን እንድታገለገልዎት በሚጠይቁት ሁሉ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ከልብ ልናገለግልዎት ዝግጁ መሆናችንን በጌታ ፈቅር እንገልጻለን።

የቤተክርስተያን ቋሚ ፕሮግራም

  • ዘወትር ዕሁድ ከ 12:00 _ 13:00 የደቀመዝሙር ትምህርት ስልጠና(ማስተር ላይፍ)
    ከ2:00 _ 4:00 የአምልኮና የቃል ግዜ
  • ዘወትር ረቡዕ ጠዋት 10:00 _ 13:00 የጾም ጸሎት ፕሮግራም
  • ዘወትር አርብ ምሽት ከ20:00 _ 21:00 የመጽሃፈ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራም (ፍሪስላንድ)
  • እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ!!

ርኆቦት ወንጌላዊት ቤተክርስትያን

Advertentie