አማርኛ ድህረ ገጽ

proclem armharic

እንኩዋን ወደ ርኆቦት ወንጌላዊት ቤተክርስትያን ለሁሉም ዜጎች አማርኛ ድህረገጽ በሰላም መጡ !

የርኆቦት ወንጌላዊት ቤተክርስትያን ለሁሉም ዜጎች የሆነች የተለያየ ዘር የተለያየ ቋንቋ እና የተለያየ ባህል ባለቤት የሆኑ የወንጌል አማኒያንን ሁሉ ያቀፈች ቤተክርስትያን ለመሆን ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች። እያንዳንዱ ማህበረሰብ እያንዳንዱ ቋንቋ እያንዳንዱ ወግ እና ባህል የራሱ የሆነ ልዩ ውበት እንዳለው ታምንናለች ። ይህንንም ግምት ውስጥ በማስገባት  ቤተክርስትያኒቷ በእግዚያብሔር ቃል ላይ በተመሰረተና  በልዩነቶች ውስጥ ያለውን ውበት በማስተናገድ ሁሉም በአንድነት የሚያመልክባት የእምነት ስፍራ ሆና ተቋቁማለች።

ቤተክርስትያኒቷ የተመሰረተችበት የእግዚያብሔር ቃል  

” …በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና…” (ትንቢተ ኢሳያስ ም56፥7)
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤….”(የማቲዮስ ወንጌል ም28፥19)
” በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥….” (የሐዋሪያት ስራ ም2፥1)
“….አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።”…. (ወደ ገላትያ ሰዎች ም3፥28)
“….አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤”…. (የዮሐንስ ራእይ 7፥9)

Advertentie